የMontgomery ካውንቲ የማህበረሰብ ግንኙነቶች የዳሰሳ ጥናት

በዚህ ጥናት ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት ስላሳዩ እናመሰግናለን።
EurekaFacts (ኢውሬካፋክትስ) ሞንትጎሜሪ ካውንቲን ወክሎ አስፈላጊ ጥናት እያካሄደ ነው።
የሞንትጎሜሪ ካውንቲ በዘማናዊ እና ተዛማጅ የሚዲያ መድረኮች አማካኝነት ጠቃሚ መረጃን ማጋራት ነው። ይህን ለማድረግ፣ የሞንትጎሜሪ ካውንቲ ኮሙኒኬሽኖችን እንዴት እንደሚያነቡ፣ እንደሚመለከቱ፣ እንደሚያገኙ፣ እንደሚሳተፉበት፣ እና እንደሚለማመዱ በተመለከተ ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን፣ የአካባቢ ዜናዎችን እና መረጃን ለመቀበል ከይዘት እና መድረክ አማራጮችዎ ጋር።
የዳሰሳ ጥናቱ ለማጠናቀቅ በግምት 15 ደቂቃዎችን የሚወስድ ይሆናል። ዳሰሳውን በመሙላት፣ እርስዎን እና ማህበረሰብዎን የሚጠቅም ዋጋ ያለው ግብረ-መልስን እያቀረቡ ነው።
ሁሉም ምላሾች ሚስጥራዊ ነው፣ እና ሪፖርት የሚደረገው ማንኛውም መረጃ ከሌሎች ምላሽች ጋር የተጣመረ ነው።
“ዳሰሳውን ጀምር” የምለው አዝራር ላይ በመጫን እድሜዎ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ እንደሆነ እና በዚህ የዳሰሳ ጥናት ውስጥ ለመሳተፍ ስምምነትዎን እንዳስመዘገቡ እያረጋገጡ ነው። በዳሰሳው ውስጥ፣ እባክዎ የዳሰሳ ጥናቱን ለመውሰድ የሚፈልጉትን ቋንቋ ይምረጡ እና ሲጠየቁ ግላዊ ኮድዎን ያስገቡ።
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
EurekaFacts ማን ነው?
EurekaFacts ኢላማ የተደረጉ ኮሙኔክሽኖችን፣ የፕሮግራም ግምገማዎችን፣ ስልታዊ ውሳኔዎችን፣ እና በውህድ-የሚሰሩ ዘዴዎችን ለመደገፍ ግንዛቤዎችን የሚሰጥ የሙሉ-አገልግሎት የጥናት እና የትንተና ተቋም ነው። እኛ የሞንትጎሜሪ ካውንቲ ኗሪዎች መካከል ይህንን ጥናት ለማካሄድ በሞንትጎሜሪ ካውንቲ ተመርጠናል።
የዚህ ጥናት ዓላማ ምንድን ነው?
ኗሪዎቹ ስለ አገልግሎቶቻቸው፣ ዜናዎች፣ ዝግጅቶች፣ ወቅታዊ ሁኔታዎች፣ እና ሌላ መረጃ በተመለከተ መረጃን ለመፈለግ እና ለመማር ስለሚጠቀሟቸው ዘርፈ-ብዙ ዘዴዎች ሞንትጎሜሪ ካውንቲ ያውቃል። ይህንን ዳሰሳ መሙላት የሞንትጎሜሪ ካውንቲ በመላው ካውንቲ ውስጥ አዲሶቹ የመግባቢያ መድረኮችን እንዲያቀናጅ እና ተገቢነት ያለው እና ትክክለኛ ይዘት በቀላሉ እንዲገኝ እንዲያረጋግጥ ይረዳል። ካውንቲው በተሻለ ሁኔታ እርስዎን ለማገልገል መረጃዎን እንዴት ለማግኘት እንደሚመርጡ እና ከካውንቲው ምን ዓይነት መረጃ እንደሚፈልጉ ማወቅ ይፈልጋል። በዚህ የዳሰሳ ጥናት ውስጥ ልምዶችዎን እና ሀሳብዎን ሲያቀርቡ እርስዎን ለሚመስሉ በሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች ይናገራሉ።
ለዚህ ጥናት እንዴት ነው የተመረጥኩኝ?
የእርስዎ ቤተሰብ በመላው ሞንትጎሜሪ ካውንቲ ካሉ እና የተለያዩ የካውንቲው አካባቢዎችን ከሚወክሉ የቤተሰቦች ዝርዝር በዘፈቀደ የተመረጠ ነው። ዳሰሳውን መሙላት እርስዎን ለሚመስሉ ሌሎች ሰዎች ውክልናን ያቀርባል።
ሌላ ቤተሰብ ዳሰሳውን እንዲሞላልኝ መጠቆም እችላለሁ?
አይ። ቤተሰብዎ ከቤተሰቦች ዝርዝር በተለየ ሁኔታ ተመርጣል። የእርስዎ ምላሽ ልዩ ነው እናም መተካት አይችልም።
መረጃዬ በሚስጥር ተይዞ ይቆያል?
ሁሉም ምላሾች ሙሉ በሙሉ በሚስጥር ይያዛሉ። ማንኛውም የሚለይ መረጃ ከማንኛውም መልሶችዎ ጋር የሚተሳሰርበት ጊዜ አይኖርም። በጥናት ሂደታችን አማካኝነት የሚሰበሰብ ሁሉም መረጃ ማንነት ሳይታወቅ አንድ ላይ ይሰበሰብ እና ሪፖርት ይደረጋል። የሞንትጎሜሪ ካውንቲ የግል ምላሾችዎ ጋ መድረስ አይችልም።
ዳሰሳውን በኢንተርኔት ብቻ መሙላት እችላለሁ?
አዎ፣ ይህ በኢንተርኔት-ብቻ የሚሞላ ጥናት ነው። እርስዎ ወይም እንዲሳተፍ የተጋበዘ የሚያውቁት ማንኛውም ሰው የኢንተርኔት ተደራሽነት ያለው ኮምፒውተር ወይም ስልክ ከሌላችሁ፣ እባክዎ በ311 ይደውሉ። የካውንቲ ተወካዮች ዳሰሳውን በኮምፒውተራቸው ላይ መሙላት ወደሚችሉት የአካባቢ ቤተመጽህፍት ይልኩዎታል።
የማህበረሰብ ግንኙነቶች የዳሰሳ ጥናቱ ካውንቲው በየሁለት ዓመቱ ከሚያደርገው የኗሪዎች የዳሰሳ ጥናት ጋር ተመሳሳይ ነው?
አይ. በየሁለት ዓመቱ የሚደረገው የዳሰሳ ጥናቱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ያሎትን የህይወት ጥራት አስመልክቶ አጠቃላይ መረጃ የሚጠይቅ ነው። ሁለት የዳሰሳ ጥናቶች ከተቀበሉ፣ እባክዎ ሁለቱንም ያጠናቅቁ እና አመሰግናለሁ!
ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉኝ ማንን ነው የሚያናግረሁ?
ለአሰራር ወይም ቴክኒካዊ ጥያቄዎች፣ እባክዎ ለ EurekaFacts በ research@eurekafacts.com ኢሜይል ይላኩ።